የውሂብ ማሰናጃ አባሪ

  1. ፍቺዎች
    በዚህ የውሂብ ማሰናጃ አባሪ ውስጥ፣ “GDPR” ማለት አጠቃላይ የውሂብ ጥበቃ ደንብ (ደንብ (EU) 2016/679)፣ እና “ተቆጣጣሪ”፣ “ውሂብ አሰናጅ”፣ “የውሂብ ባለቤት”፣ “የግል ውሂብ”፣ “የግል መረጃ መጣስ" እና "ማሰናዳት" በGDPR ውስጥ እንደተገለጸው ተመሳሳይ ፍቺዎች ይኖራቸዋል። "የተሰናዳ" እና "ስንድት" በ"ማሰናዳት" ፍቺ መሰረት መተርጎም አለባቸው። የGDPR ማጣቀሻዎች እና ድንጋጌዎቹ የተሻሻለው እና በUK ህግ ውስጥ የተካተተውን GDPR ያካትታሉ። ሁሉም ሌሎች ፍቺ የተሰጣቸው ቃላት በዚህ ስምምነት ውስጥ በሌላ ቦታ እንደተገለጹት ተመሳሳይ ፍቺ ይኖራቸዋል።
  2. ውሂብ ማሰናዳት
    1. በውሂብዎ ውስጥ ካለ ማንኛውም የግል መረጃ (‹‹የእርስዎ የግል ውሂብ››) ጋር በተገናኘ በዚህ ስምምነት ስር እንደ አሰናጅ ተግባራቶቹን ሲያከናውን Meta ይህንን ያረጋግጣል፦
      1. የማሰናዳቱ ቆይታ፣ ርዕሰ ጉዳይ፣ ተፈጥሮ እና ዓላማ በስምምነቱ ውስጥ በተገለፀው መሠረት ይሆናል፤
      2. የተሰናዱ የግል ውሂብ ዓይነቶች በእርስዎ ውሂብ ፍቺ ውስጥ የተገለጹትን ያካትታሉ፤
      3. የውሂብ ባለቤቶች ምድቦች የእርስዎን ተወካዮች፣ ተጠቃሚዎች እና ሌሎች በእርስዎ የግል ውሂብ ተለይተው የሚታወቁ ወይም የሚለዩ ግለሰቦችን ያጠቃልላል፤ እና
      4. ከግል ውሂብዎ ጋር በተያያዘ እንደ የውሂብ ተቆጣጣሪ የእርስዎ ግዴታዎች እና መብቶች በዚህ ስምምነት ውስጥ በተገለጸው መሰረት ናቸው።
    2. Meta የእርስዎን የግል ውሂብ በስምምነቱ ስር ወይም ከስምምነቱ ጋር በተያያዘ እስካሰናዳ ድረስ Meta የሚከተሉትን ያደርጋል፦
      1. በGDPR አንቀጽ 28(3)(a) ለተፈቀዱ ልዩ ሁኔታዎች ተገዢ ሆኖ፣ የግል ውሂብዎን ማስተላለፍን ጨምሮ በዚህ ስምምነት ስር በተገለጸው መመሪያዎ መሰረት ብቻ የእርስዎን የግል ውሂብ ያሰናዳል፤
      2. በዚህ ስምምነት መሰረት የእርስዎን የግል ውሂብ ለማስኬድ ስልጣን የተሰጣቸው ሰራተኞቹ ወደ ለሚስጥራዊነት ቁርጠኛ መሆናቸውን ወይም ከግል ውሂብዎ ጋር በተገናኘ አግባብ ባለው ህጋዊ ሚስጥር የመጠበቅ ግዴታ ውስጥ መሆናቸውን ያረጋገግጣል፤
      3. በውሂብ ደህንነት አባሪ ውስጥ የተቀመጡትን ቴክኒካዊ እና ድርጅታዊ እርምጃዎችን ይተገብራል፤
      4. ንዑስ አሰናጆችን በሚሾምበት ጊዜ በዚህ የውሂብ ማሰናጃ አባሪ ክፍል 2.c እና 2.d ውስጥ የተጠቀሱትን ሁኔታዎች ያከብራል፤
      5. በWorkplace ይህ እስከተቻለ ድረስ፣ በGDPR ምእራፍ III መሰረት ከውሂብ ባለቤቶች ለሚቀርብ መብቶችን እንድያከብር የሚያሳስብ ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት አንጻር ግዴታዎትን እንዲወጡ በተገቢ የቴክኒክ እና አደረጃጀት እርምጃዎች አማካኝነት ያግዞታል፤
      6. የማሰናዳቱ ባህሪይ እና Meta ማግኘት የሚችለውን መረጃ ከግምት በማስገባት በGDPR አንቀጽ 32 እስከ 36 መሰረት ግዴታዎትን እንዲወጡ ያግዞታል፤
      7. ስምምነቱ ሲቋረጥ፣ የአውሮፓ ህብረት ወይም የአባል ሀገራት ህግ የግል ውሂብ እንዲቆይ ካላደረገ በስተቀር፣ በስምምነቱ መሰረት የግል መረጃውን ይሰርዛል፤
      8. በአንቀጽ 28 GDPR መሠረት የMeta ግዴታዎች መከበራቸውን ለማሳየት አስፈላጊ የሆኑትን ሁሉንም መረጃዎች ለማቅረብ Meta ያለውን ግዴታ በማርካት በዚህ ስምምነት ውስጥ የተገለፀውን መረጃ እና በWorkplace በኩል ለእርስዎ ያቀርባል፤ እና
      9. በየአመቱ የMeta ምርጫ ሶስተኛ ወገን ኦዲተር ከWorkplace ጋር በተገናኘ የMetaን ቁጥጥር የSOC 2 Type II ወይም ሌላ የኢንዱስትሪ ደረጃ ኦዲት እንዲያደርግ ይገዛል፣ የሶስተኛ ወገን ኦዲተር በእርስዎ የታዘዘ ነው። እርስዎ ጥያቄ ሲያቀርቡ፣ Meta በወቅቱ የሚኖረውን የኦዲት ሪፖርቱን ቅጂ ይሰጥዎታል፤ እና እንዲህ አይነት ሪፖርት የMeta ምስጢራዊ መረጃ ተደርጎ ይቆጠራል።
    3. Meta በዚህ ስምምነት ስር ያሉትን ውሂብ የማሰናዳት ግዴታዎች ለMeta ተባባሪዎች እና ለሌሎች ሶስተኛ ወገኖች በንኡስ ኮንትራት እንዲሰጥ ፍቃድ ሰጥተዋል፤ የእነዚህ ዝርዝራቸውም እርስዎ በጽሁፍ ሲጠይቁ Meta ይሰጥዎታል። Meta ይህን የሚያደርገው በዚህ ውል መሠረት በMeta ላይ የተጣሉትን የውሂብ ጥበቃ ግዴታዎች በንዑስ አሰናጁ ላይ በሚጥል ከንዑስ አሰናጁ ጋር በሚደረግ የጽሁፍ ስምምነት ብቻ ነው። ንዑስ-አሰናጅ እንዲህ ያሉ ግዴታዎችን ሳይፈጽም ሲቀር፣ Meta ለንዑስ-አሰናጁ የውሂብ ጥበቃ ግዴታ አፈጻጸም ሙሉበሙሉ ተጠያቂ ይሆናል።
    4. Meta (i) ከግንቦት 25 ቀን 2018 ወይም (ii) ከሚፀናበት ቀን (የኋለኛው የትኛውም ይሁን) ተጨማሪ ወይም ተተኪ ንዑስ አሰናጅ(ጆች) ሲያሳትፍ፣ እንዲህ አይነት ተጨማሪ ወይም ተተኪ ንዑስ አሰናጅ(ጆች)ን Meta ተጨማሪ ወይም ምትክ ንዑስ አሰናጅ(ጆች) ከመሰየማቸው ከአስራ አራት (14) ቀናት በፊት አስቀድሞ ያሳውቅዎታል። Meta መረጃውን ባደረሰዎት በአስራ አራት (14) ቀናት ውስጥ እንደዚህ ያሉ የተጨማሪ ወይም ተተኪ ንዑስ አሰናጅ(ጆች) መሳተፍን ለMeta የጽሁፍ ማሳወቂያ በመላክ ወዲያውኑ ስምምነቱን በማቋረጥ መቃወም ይችላሉ።
    5. ከግል ውሂብዎ ጋር የተገናኘ የግል ውሂብ መጣስ እንዳለ ሲያውቁ Meta ያለአንዳች መዘግየት ያሳውቅዎታል። እንዲህ ዓይነቱ ማሳወቂያ፣ በማሳወቂያው ጊዜ ወይም በተቻለ ፍጥነት ማሳወቂያ ከተሰጠ በኋላ፣ ከተቻለ የግል ውሂብ መጣስ አስፈላጊ ዝርዝሮች፣ የተጎዱ መዝገቦችዎ ብዛት፣ የተጎዱ ተጠቃሚዎች ምድብ እና ግምታዊ ቁጥር፣ ከጥሰቱ የሚጠበቁ ውጤቶችን እና ጥሰቱ ሊያስከትላቸው የሚችሉትን አሉታዊ ተፅእኖዎች ለመቀነስ ማንኛውም ትክክለኛ ወይም የታቀዱ መፍትሄዎች ያካትታል።
    6. GDPR ወይም በEEA፣ UK ወይም ስዊዘርላንድ ያሉት የውሂብ ጥበቃ ሕጎች በዚህ የውሂብ ማሰናጃ አባሪ ስር ባለው የእርስዎ ውሂብ ስንድት ላይ ተፈጻሚ እስከሆነ ድረስ፣ የአውሮፓ የውሂብ ማስተላለፍ አባሪ በMeta Platforms አየርላንድ ሊሚትድ የውሂብ ሽግግሮች ላይ ተፈፃሚነት ይኖረዋል፤ የዚህ የውሂብ ማሰናጃ አባሪ አካል እና በማጣቀሻነትም የተካተተ ሆኗል።
  3. USA የአሰናጅ ደንቦች
    1. የMeta USA የአሰናጅ ደንቦች ተፈጻሚ እስከሆኑ ድረስ የዚህ ስምምነት አካል እና በማጣቀሻነት የተካተቱት ይሆናሉ፣ ለክፍል 3 (የኩባንያው ግዴታዎች) በግልጽ ያልተካተተ ነው።